ጃንጥላቶክስ | JantillaTalks
Date and time
Location
DoubleTree by Hilton Hotel - Silver Spring
8727 Colesville Road
Silver Spring, MD 20910
Refund policy
Contact the organizer to request a refund.
Eventbrite's fee is nonrefundable.
ጃንጥላቶክስ አሁንም እጅግ ውብ፣ አስተማሪና አዝናኝ ኮንፈረንስ አዘጋጅቷል። Saturday, Nov 02, 2019. *3:00 PM at the DoubleTree by Hilton Hotel - Silver Spring, MD.
About this event
JantillaTalks will host its semiannual conference on Saturday, Nov 02, 2019, at the DoubleTree by Hilton Hotel - Silver Spring, MD.
Jantilla Inc., headquartered in Maryland, USA, strives to serve as a platform to preserve and disseminate societal values, knowledge creation and experience sharing on a wide range of topics that matter to the public discourse in the Ethiopian Diaspora and beyond.
*************************
በጃንጥላቶክስ አሁንም እጅግ ውብ፣ አስተማሪና አዝናኝ ኮንፈረንስ ተዘጋጅቷል። ይህ ዝግጅት ሲሊቨር ስፕሪንግ በሚገኘው የደብል ትሪ ሂልተን ሆቴል ኖቬምበር 2፣ 2019 ከ3:00 PM ጀምሮ ይካሄዳል።
ሁልጊዜም እንደምናደርገው የዚህ ኮንፈረንስ ተናጋሪዎችም በሀገርና ዓለም አቀፍ ደረጃ በርካታ አስተዋዕጽኦ ያደረጉ ተጽእኖ ፈጣሪ ምሁራን ናቸው። ከዋና ተናጋሪዎች አንዱ የሆኑት ሙሐዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት በታሪክ ምርምር፣ በሥነ-ጽሑፍ፣ በባሕል፣ በፍልስፍና ለሀገር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከቱ ሰው ናቸው። ሙሐዘ ጥበባት ዳንኤል ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ካላቸው ፍቅር የተነሳ ዕውቀታቸውንና ጊዜያቸውን ሳይሳሱ በመለገስ እጅግ ብዙ ስራዎችን ሰርተዋል፣ አሁንም በመስራት ላይ ይገኛሉ። የበጎ ሰው ሽልማት ድርጅት መስራችና ዳይሬክተርም ናቸው። በታሪክ፣ በወግ፤ በባሕል፣ በፍልስፍናና ሐይማኖት ዘርፍ በርካታ መፅሐፍትን ፅፈው ከማበርከታቸውም በተጨማሪ በአያሌ መድረኮች ላይ ንግግር በማድረግም ይታወቃሉ። ጃንጥላቶክስ ሙሐዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረትን በዋና ተናጋሪነት ለዚህ ኮንፍረንስ ያቀርብለዎታል።
ሌላው ተናጋሪ አቶ ኤልያስ ወንድሙ ናችው። አቶ ኤልያስ ዓለማቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ህትመት የሚሰራና በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ የሆነው የፀሀይ አሳታሚ ድርጅት መስራችና ዋና ሥራ አስኪያጅ ሲሆኑ በኢትዮጵያ የታሪክ ሽግግር ከፍተኛ ጠቀሜታ ያላቸውን ከ150 ባላይ መፅሕፍትን አሳትመው ለስርጭት አብቅተዋል። ከማተሚያ ቤቱ በተጨማሪ ዕድሜያቸውን በሙሉ ለወገን እርድታ በማዋል በበርካታ ሰብአዊ እርዳታዎቻቸውም ይታወቃሉ።